የምርጫ ካርድ የዲሞክራሲ መብታችን ማስከበሪያ መሣሪያችን ነው"
22 Apr 2026
የምርጫ ካርድ የዲሞክራሲ መብታችን ማስከበሪያ መሣሪያችን ነው"
22 Apr 2026
"የምርጫ ካርድ የዲሞክራሲ መብታችን ማስከበሪያ መሣሪያችን ነው" - ዜጎች
****************
በኢትዮጵያ የፊታችን ግንቦት 24 ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሲከናወን የቆየው የመራጮች ምዝገባ በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።
እስካሁን ባለው የዘንድሮው የመራጮች ምዝገባ ሂደት ከ46 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የምርጫ ካርዳቸውን ወስደዋል። የምዝገባው ማብቂያ ቀን መቃረቡን ተከትሎ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ የመራጭነት ካርዳቸውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ የኢቢሲ ዶት ስትሪም ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፣ የምርጫ ካርድ መያዝ የሀገርን የወደፊት አቅጣጫ ለመወሰን ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ያለው አንድ ቀን ሳይረፍድባቸው ዜጎች ይህ ዕድል ስለማይደገም "ይበጀኛል፣ የሀገራችንን ራዕይ ያሳካል" የሚሉትን እንዲመርጡ ሐሳባቸውን ሰጥተዋል።
ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በተለየ መልኩ፣ ዘንድሮ ዜጎች የምርጫ ካርድ የሚወስዱባቸው እና የሚመዘገቡባቸው አማራጮች ወደ ዲጂታል አሰራር ከፍ ማለቱ የምዝገባ ሂደቱን ይበልጥ ቀልጣፋ እና ተደራሽ እንዳደረገውም ጠቁመዋል።
በ'ምርጫዬ' የሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት ዜጎች በቀላሉ ካሉበት ቦታ ሆነው መመዝገብ መቻላቸውንም ነው የገለጹት።

ተጨማሪ ምስሎች