Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

ዋና ገጽ ዜናዎች አገልግሎቶች ስለ እኛ አግኙን
ወደ ዜናዎች ተመለስ

በፀደይ እርጥበት የተዘራው የሽምብራ ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ተገለፀ።

20 Nov 2025
በፀደይ እርጥበት የተዘራው የሽምብራ ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ተገለፀ።

በፀደይ እርጥበት የተዘራው የሽምብራ ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ተገለፀ።

20 Nov 2025

በፀደይ እርጥበት የተዘራው የሽምብራ ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ተገለፀ።

(ወልቂጤ) ኅዳር 10/2018 ዓ.ም
በቀቤና ልዩ ወረዳ በፀደይ እርጥበት የተዘራ የሽምብራ ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ በኩታ ገጠም በስፋት ከሚመረቱ ሰብሎች መካከል ጤፍ፣ በቆሎ አና ሽምብራ ይገኙበታል።

በመኸር ወቅት በ12 ሺህ 6 መቶ ሄክታር ላይ በኩታ ገጠም ከተመረተ በቆሎ በተጨማሪም ቦለቄ እና ሌሎች ሰብሎች በማንሳት በልዩ ወረዳው በጠቅላላ 15 ሺህ 2 መቶ ሄክታር ማሳ የአፈሩን እርጥበት በመጠቀም በኩታ ገጠም በሽምብራ ተሸፍኗል።

በሽምብራ ማሳቸው ላይ አረም ሲያርሙ አግኝተን ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት፣ የበቆሎ ሰብላቸውን በማንሳት የመሬቱን እርጥበት ብቻ በመጠቀም ያለምንም ማዳበሪያ እና መስኖ በየዓመቱ ሽምብራ ማምረት መቻላቸው ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው ገልፀው፣ የዘንድሮው የሽምብራ ሰብልም በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል።

አርሶ አደሮቹ ሽምብራ በተባይ የመጠቃት እድል እንዳለው ገልፀው ለዚህ ደግሞ የግብርና ባለሙያዎች በቅርበት ክትትል በማድረግ ችግሩ ሲከሰት የፀረ-ተባይ መድሃኒት አቅርቦት በማመቻቸት እና አጠቃቀሙ ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ድጋፍ የሚያደርጉላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የፈረጀቴ ቀበሌ ድጋፍ ሰጪ የግብርና ባለሙያ የሆኑት አቶ መሐመድአሚን ሸምሱ በሰጡት አስተያየት አርሶ አደሩ የቦቆሎ ሰብሉን በማንሳት የመሬት እርጥበትን ተጠቅሞ ሽምብራ ማምረት መቻሉ ተጠቃሚ የሚሆነው በኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን፣ በቆሎ አንስቶ ሽምብራ መተካት ክሮፕ ሮቴሽን ስለሚኖር ማሳውን ለቀጣይ እርሻ ከማዘጋጀቱም ቀላይ የመሬቱ ምርታማነት እንዳይቀንስ ያደርጋል ብለዋል።

እንደ ቀቤና ልዩ ወረዳ "የአፍሪካ የጓያ ትል" ሽምብራው በሚያብብበት ወቅት የሚያጠቃ እና ምርታማነትን የሚቀንስ መሆኑን ገልፀው፣ ችግሩ ተከስቶ ጉዳት ሳያስከትል ለመቆጣጠር የማሳ ምልከታ በማድረግ ክትትል የሚደረግ መሆኑን አንስተው፣ ችግሩ ከተከሰተም ከህጋዊ አቅራቢ ድርጅቶች ትክክለኛውን ፀረ-ተባይ ተጠቅመው ርጭት እንዲያደርጉ ቴክኒካል ድጋፎችን የሚያደርጉ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ መሐሀመድአሚን ሸምሱ በፈረጀቴ ቀበሌ ብቻ ከ2 ሺህ ሄክታር ባላይ ሽምብራ በኩታ ገጠም ማሳ መዘራቱን ገልፀው፣ በአማካኝ በሄክታር 25 ኩንታል ምርት ለማግኘት እንደሚጠብቁም ተናግረዋል።

******************

ተጨማሪ ምስሎች