Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

ዋና ገጽ ዜናዎች አገልግሎቶች ስለ እኛ አግኙን
ወደ ዜናዎች ተመለስ

የልዩ ወረዳውን የውሃ ሽፋን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቀቤና ልዩ ወረዳ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ፅ/ቤት ገለፀ፡፡

28 Oct 2025
የልዩ ወረዳውን የውሃ ሽፋን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቀቤና ልዩ ወረዳ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ፅ/ቤት ገለፀ፡፡

የልዩ ወረዳውን የውሃ ሽፋን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቀቤና ልዩ ወረዳ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ፅ/ቤት ገለፀ፡፡

28 Oct 2025

የልዩ ወረዳውን የውሃ ሽፋን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ፅ/ቤት ገለፀ፡፡

ወልቂጤ፣ ጥቅምት፣ 18/2018 ዓ.ም

ጽ/ቤቱ ከቀቤና ልማት ማህበርና "ቢሩ ረህማ ሚን አህለል ኢምሬት" ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ጽርጅት ጋር በመተባበር በልዩ ወረዳው በልንጫ ቀበሌ በ2.5 ሚልየን ብር የተገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡

የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድአሚን በደዊ በዚህ ወቅት እንደገለፁት የዉሃ ግንባታው ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠርና የልዩ ወረዳውን የውሃ ሽፋን ለማሳደግ የጎላ አስተዋጽኦ አለው፡፡

በቀጣይም በልዩ ወረዳው የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ተደራሽነት ለማሻሻል ከግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንደሚሰራ አቶ መሀመድአሚን ተናግረዋል ፡፡

የቀቤና ልዩ ወረዳ የቀድሞ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ በበኩላቸው የልዩ ወረዳውን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ውጤታማነት ምቹ እድል የሚፈጥሩ የከርሰ ምድርና ሌሎችም በርካታ የዉሃ አማራጮች በመኖራቸው በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡

በልዩ ወረዳው በሁሉም ዘርፍ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ከግብ እንዲደርስ ሁሉም በያለበት በትብብርና በጋራ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል ፡፡

የልዩ ወረዳው ውሃ ማዕድንና ኤነርጂ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጁሃር ጀማል የልዩ ወረዳውን የውሃ ሽፋን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ ገና ብዙ ስራ እንደሚጠይቅ ገልፀው በዕለቱ የተመረቀው የውሃ ግንባታ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም በአካባቢው የነበረውን የንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት ችግር የሚቀርፍ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡

ለዚህም ፕሮጀክቱን ለአስተባበሩና ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ጁሃር በቀጣይም ከግብረሰናይ ድርጅቶችና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ዳውድ ተማም የፕሮጀክቱ አስተባባሪና የጅማ ዩንቨርስቲ መምህር ሲሆኑ የውሃ ፕሮጀክቱ በጥራትና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መገንባቱን ጠቁመዋል፡፡

ፕሮጀክቱ 2.5 ሚልየን ብር መፍጀቱንና ከ1500 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚችልም ተናግረዋል ፡፡

ከዚህ ቀደም በአካባቢው የንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት ባለመኖሩ ውሃ ፍለጋ ረጅም ርቀት ለመሄድ ይገደዱ እንደነበረ የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች አሁን ላይ ችግሩ በመቀረፍ መደሰታቸውን ገልፀዋል ፡፡

****************

ተጨማሪ ምስሎች