Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

ዋና ገጽ ዜናዎች አገልግሎቶች ስለ እኛ አግኙን
ወደ ዜናዎች ተመለስ

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው :-ወ/ሮ ፈቲያ ሱልጣን

26 Oct 2025
የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው :-ወ/ሮ ፈቲያ ሱልጣን

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው :-ወ/ሮ ፈቲያ ሱልጣን

26 Oct 2025

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው :-ወ/ሮ ፈቲያ ሱልጣን

(ወልቂጤ፣ጥቅምት 16/2018) የቀቤና ልዩ ወረዳ ሴቶች ህጻናት ጽ/ቤት የሩሙጋ ቀበሌን ለሁለተኛ ዙር በሴቶች የልማት ህብረት ሞዴልነት አስመረቀ ።

የልዩ ወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ ሱልጣን በልዩ ወረዳው በሴቶች የልማት ሕብረት በርካታ ተስፋ ሰጪ ስራዎች መሰራት መቻላቸውን ገልጸው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም የሴቷን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎችን፣ ሀብት የመፍጠርና የመለወጥ አስተሳሰቦችን ደግፈን መስራት ከቻልን በልዩ ወረዳው በሁሉም ቀበሌያት ሞዴል የሴቶች ልማት ሕብረትን በመፍጠር ለሌላው አከባቢ አርአያ መሆን እንደሚቻል አመላክተዋል።

የልዩ ወረዳው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፋጤ ሰማን በበኩላቸው ሴቶች በሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ ላይ
ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በየደረጃው ያለው ባለድርሻ ሴቶችን እያገዘየሚሄድ ከሆነ ሴቶች የመከወን ብቻ ሳይሆን ውጤታማ የመሆንም አቅማቸው ከፍተኛ በመሆኑ እንደሀገር ያለው ፋይዳም የጎላ ነው ብለዋል።

በቀበሌው በሴቶች የልማት ህብረት የተሰሩ የሌማት ትሩፋት ስራዎች ፣ የሴቶች ልማት ሕብረት የቤት ለቤት እቅድ ትግበራ መረጃ አያያዝና አጠቃቀም ፣የአካባቢ ንጽህናና የመጸዳጃ ቤት አያያዝ አካላዊ ምልከታ ተደርጓል።

በመጨረሻም በቀበሌው ውስጥ ለሚገኙ የልማት ህብረቶችና ለስትሪንግ ኮሚቴ አባላት የዕውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት በመስጠት የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተጠናቋል።

በፕሮግራሙ ላይ የልዩ ወረዳው የሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ ሱልጣን፣ የልዩ ወረዳው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፋጤ ሰማን፣ የቀበሌው አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

**********

ተጨማሪ ምስሎች