Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

ዋና ገጽ ዜናዎች አገልግሎቶች ስለ እኛ አግኙን
ወደ ዜናዎች ተመለስ

በቀቤና ልዩ ወረዳ መደበኛ ክትባት ሳይከተቡ ላመለጣቸው ህፃናት የክትባት ዘመቻ በሩሙጋ ቀበሌ ተጀምሯል ።

23 Oct 2025
በቀቤና ልዩ ወረዳ መደበኛ ክትባት ሳይከተቡ ላመለጣቸው ህፃናት የክትባት ዘመቻ በሩሙጋ ቀበሌ ተጀምሯል ።

በቀቤና ልዩ ወረዳ መደበኛ ክትባት ሳይከተቡ ላመለጣቸው ህፃናት የክትባት ዘመቻ በሩሙጋ ቀበሌ ተጀምሯል ።

23 Oct 2025

በቀቤና ልዩ ወረዳ መደበኛ ክትባት ሳይከተቡ ላመለጣቸው ህፃናት የክትባት ዘመቻ በሩሙጋ ቀበሌ ተጀምሯል ።

ወልቂጤ ፣ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቀቤና ልዩ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በልዩ ወረዳው በሩሙጋ ቀበሌ የተቀናጀ የጤና ስራ እና ክትባት ያልተከተቡና ጀምረው ያቋረጡ ህፃናትን ክትባት መስጠት ጀምሯል ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህክምና አገልግሎት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር የሆኑት ዶ/ር ዳዊት ዳንኤል እንደገለፁት ከጥቅምት 13- 22/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 10 ቀናት በሚደረገው የተፋጠነ እና ታላሚ ተኮር የማካካሻ ክትባት ዘመቻ በዋናነት በክልሉ 102,122 ክትባት አገልግሎት ላላገኙ ፣ 945,00 ክትባት ጀምረው ላቋረጡ እንዲሁም 193,309 ተከታታይ የኩፍኝ ክትባት ያመለጣቸውን ህፃናት ለማድረስ የተዘጋጀ እንደሆነ ጠቁመዋል።

እንደ ቀቤና ልዩ ወረዳ 771 ያልተከተቡ ፣ 102 ጀምረው ያቋረጡ እንዲሁም ከ2,000 በላይ ተከታታይ የኩፍኝ ክትባት ያልወሰዱ ህፃናትን በዘመቻው ለመከተብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ ክትባቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።

ኃላፊው አክለውም ከክትባቱ ጎን ለጎን የወባ መከላከልና መቆጣጠር፣ የማህፀን ውልቃትና መሸንቆር ልየታ፣ የማህፀን በር ካንሰር ልየታና ህክምና እንዲሁም የከፋ የምግብ እጥረት ልየታና ህክምና ለህፃናት፣ ለነፍሰጡር እና አጥቢ እናቶች እንደሚደረግ ተናግረዋል ።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሀይ ኑርሀሰን እንደተናገሩትም የዛሬው ዘመቻ እንደ ሀገርና ክልላችን የተቀናጀ የክትባት አገልግሎት ዘመቻ የተከፈተበት ቀን መሆኑን በመጠቆም በልዩ ወረዳው በ24ቱም ቀበሌዎች ለተከታታይ 10ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል ።

********
በፀጋዬ አረጋ

**
#ውጤታማ የመረጃ ልውውጥ ለልማት !

ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ይጠቀሙ‼️

👉Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100072292788562&mibextid=ZbWKwL
👉Instagram https://www.instagram.com/qebenacomm?igsh=NHRiZjFybHk4dmRn

👉Twitter https://x.com/KebenaO88374?t=T_ncptfwuNAwRnhxrqdM9w&s=09

👉Telegram channel
https://t.me/Qebena1

👉youtube
https://youtube.com/@kebenaspecialworedacomm?si=DOrrIJYDBKMzjXCr

👉tiktok
tiktok.com/@kebenacommunication
👉email :- kebenaworedacommunicationaffai@gmail.com

ተጨማሪ ምስሎች