Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

ዋና ገጽ ዜናዎች አገልግሎቶች ስለ እኛ አግኙን
ወደ ዜናዎች ተመለስ

የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድርክ በወልቂጤ ከተማ አካሄደ።

23 Oct 2025
የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድርክ በወልቂጤ ከተማ አካሄደ።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድርክ በወልቂጤ ከተማ አካሄደ።

23 Oct 2025

የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድርክ በወልቂጤ ከተማ አካሄደ።

ወልቂጤ ጥቅም 13/2018 ዓ.ም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር1395/2017 ዙርያ ለፅ/ቤት ሰራተኞች፣ለልዩ ወረዳው ግብር ከፉዮች እና ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ የማስጨበጫ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል።

በመድረኩ የተገኙት የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ በሀሩ ዲጋ እንደገለፁት በአዲሱ አዋጅ ዙርያ እንደ ሀገር መድረክ ተፈጥሮ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑ ገልፀው አዋጁ በታክስ ግብር በፍቃደኝነትና በታማኝነት የመክፈል ባህል እንዲዳብር የሚያግዝ መሆኑን በመናገር የልዩ ወረዳው የንግዱ ማህበረሰብ መብትና ግዴታውን እንዲረዳና የገቢ አፈፃፀሙ ውጤታማ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

አዋጁ እንደ ሀገር የገቢ አቅምን ለማሳደግና ፍትሀዊ የግብር አከፋፈል ስርአትን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን በመጠቆም አሁን በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ላይ የልዩ ወረዳው የንግዱ ማህበረሰብ ግንዛቤውን በማሳደግ በታማኝነት ግብር መክፈል እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።

በተጨማሪም የንግዱ ማህበረሰብ እንደየንግድ ድርጅቶቻቸ አየነትና ባህሪ የውሎ ሽያጭ ሁኔታ ተከታትለው በመመዝገብ በተገቢው እና በወቅቱ ግብር በመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የፅ/ቤቱ የገቢ ጥናት የታክስ ኮሚኒኬሽን ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀሀይ ካሳ በበኩላቸው እንደተናገሩት ሀገር የምትገነባው ዜጎች በሚከፍሉት ግብር መሆኑን አስረድተው በልዩ ወረዳውም የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ለመስራት ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ግብርን በወቅቱ የመክፈል ባህሉን ሊያጠናክር ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ለግንዛቤ ማስጨበጫ በቀረበው ሰነድ መነሻነት ከባለድርሻ አካላት ሀሳብ አስተያየት የተነሳ ሲሆን ለተነሱት ሀሳብና አስተያየቶችም በፅ/ቤቱ ሀላፊዎች እና በማኔጅመት አካላት ምላሽና ማብራሪያ በመስጠትና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫን በማመላከት ተመላክቷል ተጠናቋል ።

*******
በሙከረም አለዊ
********************
#ውጤታማ የመረጃ ልውውጥ ለልማት !!
****************************
ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ይጠቀሙ‼️

👉Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100072292788562&mibextid=ZbWKwL

👉Instagram https://www.instagram.com/qebenacomm?igsh=NHRiZjFybHk4dmRn

👉Twitter https://x.com/KebenaO88374?t=T_ncptfwuNAwRnhxrqdM9w&s=09

👉Telegram channel
https://t.me/Qebena1

👉youtube
https://youtube.com/@kebenaspecialworedacomm?si=DOrrIJYDBKMzjXCr
👉tiktok
tiktok.com/@kebenacommuni

ተጨማሪ ምስሎች